Ethiopian Institute of Agricultural Research logo Jimma Agricultural Research CenterJimma
JARC · News

የተሻሻለ የቡና ችግኝ አመራረትና የችግኝ ጣቢያ አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ

Nov 26, 2026 Jimma 2 min read
የተሻሻለ የቡና ችግኝ አመራረትና የችግኝ ጣቢያ  አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ
የተሻሻለ የቡና ችግኝ አመራረትና የችግኝ ጣቢያ አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ .................................. ጥራት ያለው ችግኝ፣ ለተሻለ የቡና ምርት መሠረት ነው። የቡና ልማት ሲታሰብ መሰረቱ የሚጣለው ከችግኝ ጣቢያ ነው። የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል በየአመቱ በዘር፣ በቲሹ ካልቸርና በቁርጥራጭ የቡና ችግኞችን እያባዛ ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ የሚገኝ ተቋም ነው። በምርምር ተቋሙ የሚባዙ ችግኞች የቡና አብቃይ አርሶ አደሮችን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ማሟላት እንደማይቻል ይታወቃል። በምርምር፣ በግብርና ቢሮ እና በለለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ከሚባዙ ችግኞች በተጨማሪ አርሶ አደሮች በግልና በቡድን በማደራጀት የቡና ችግኝን ማባዛት ያስፈልጋል። የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል በደቡብ ኦሮሚያ ዞን በማና፣ በሰቃ፣ በሸቤ ሶምቦና ኦሞ ናዳ ወረዳወች አርሶ አደሮችን በግልና በቡድን በማደራጀት ለ2019 ዓ/ም የቡና ተከላ ወቅት ቡናን በብዛት እንዲያባዙ የቡና ዘር እና የችግኝ ጣቢያ ግብአቶችን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ የምርምር ማዕከሉ ከስፔን አለም አቀፍ የልማት ትብብር (AECID) በ SGCCI ፕሮጀክት ድጋፍ በቡድን ለተደራጁ ሴትና ወጣት አርሶ አደሮች እንዲሁም በግል የቡና ችግኝን ለሚያዘጋጁ አርሶ አደሮች ስለ ዘመናዊ የቡና ችግኝ አመራረት እና ስለ ዘመናዊ የቡና ችግኝ ጣቢያ አያያዝ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠናዎችን ህዳር 4 እና 8/2019 ዓ/ም ሰጥቷል። በተጨማሪም አርሶ አደሮች ግብርናን ወደ ቢዝነስ መቀየር የሚያስችላቸውን እውቀት እንዲያገኙ ስለ መሰረታዊ የቢዝነስ ጽንሰ ሃሳብና የገበያ መርሆች ዙርያ ስልጠና ተሰጥቷል። ...................................

Training Provided on Improved Coffee Seedling production and nursery Management ……………………………………………………………… Successful coffee production begins in the nursery. Each year, the Jimma Agricultural Research Centre (JARC) provides coffee seedlings for coffee producers using various propagation methods, such as seeds, tissue culture and stem cuttings. However, seedlings produced by research centres alone cannot fully meet the growing demand from coffee-producing farmers. Therefore, it is essential to strengthen farmers’ capacity to produce their own coffee seedlings in order to expand coffee production and ensure a sustainable supply of quality planting materials. Jimma Agricultural Research Centre is supporting farmers in Mana, Seka, Shebe Sombo and Omo Nada districts to establish and strengthen individual and group-based coffee seedling production. The centre is providing coffee seeds and nursery materials to enable farmers to multiply coffee seedlings for 2027 (2019 E.C.) coffee planting season. Jimma Agricultural Research Centre provided both theoretical and practical training for youth groups and farmers in Mana, Seka, Shebe Sombo and Omo Nada districts with the support of the Spanish Agency for International Development Cooperation (AECID) SGCCI Project on 13th and 16th November 2026. The training programme covered coffee seedling production, nursery management, and basic business concepts. ........................... #JARC #AECID #SGCCI #EIAR #Seedlingproduction #Coffee #Seedling #Coffeeseed #Youth #Women

Back to News