COVID-19 Response
 

ኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ 110ኛ በአገራችን ደግሞ 45ተኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በእንስቲትዩቱ ዋናው መስሪያ ቤት ህሩይ አዳራሽ  ”በኮቪድ-19 ተጽዕኖ ውስጥም የሴቶች የአመራር እኩልነትን ማምጣትበሚል  መሪቃል  ተከብሮዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሚዩኒኬሽን   ዳይሬክተር አቶ ደረሰ ተሾመ የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመግቢያ ንግግራቸውም ላይ እንደምርምር ተቋም ቀኑን ስናከብር ሴቶች በመሀበራዊ ኑሮ፤ በኢኮኖሚና በምርምሩ ዘርፍ ያበረከቱትን ሁለንተናዊ ሚና በመዘከር ነው ብለዋል፡፡ ወደ ፊትም ሴቶች ያለባቸውን የቤተሰብ ጫና በማቃለል በምርምሩ ወደፊት እንዲመጡ   በመደገፍ ወደመሪነት ለማብቃት  ማገዝ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን፤ በተጨማሪም ሴቶችን ማክበር ብሎም እራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ለራስ አጋዣ መፍጠር እናራስን ማክበር ነው ብለዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የስርአተ ጾታ ምርምር አስተባባሪ የሆኑት ወይዘሮ ለምለም አበበ ደግሞ የዘንድሮውን የሴቶች ቀን ስናከብር ከሌላው ጊዜ በተለየ ነው ያሉ ሲሆን ይኸውም ካለብን የስራ ሀላፊነት በተጨማሪ የኮቪ19  ወረርሽኝን   በመቋቋም ቤተሰባችንን እና መሀበረሰባችንን ከወረርሽኙ ለመታደግ ብሎም ስርጭቱን ለመግታት ተጨማሪ ትጋትና ጉልበት በተጠየቅንበት ወቅት ላይ ማክበራችን  ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም እንደምርምር ተቋም ሴቶችን በዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት በማጎልበት በአመራር ቦታ በእኩልነት ማሳተፍ ለሀገር እድገት ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ጨምረውገልጸዋል፡፡

 

በፕሮግራሙ ላይ በኮሚዩኒኬሽን ዳይሬተር  ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ባሲሊዎስ መነሻ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን    ከበአሉ ታዳሚዎች ጋር የፓናል  ውይይት ተካሂደዋል፡፡ በውይይቱም ላይ በስርአተ ጾታ ዙር ያ የግንዛቤ ማስበጫ ስራ በመስራትየተለያዩ የድራማ እና የስነ-ጽሁፍ ዝግጅቶችን በማድረግ ተከብሯል፡፡

 

በመጨረሻም በዓሉን በየጊዜው ቀኑን ጠብቆ ማክበር ብቻ ሳይሆን በሀገራችን ሴቶች ያሉባቸውን የመብት፤ የእኩልነት፤ የሀብትና የሰላም እጦት ችግሮችን በመፍታት መሆን ይኖርበታል፡፡ ለሴቶችና ህጻናት ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁልጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ድህነት እና ችግርን በማጥፋት  ልንሰራ ይገባል ፡፡  ሌላው የሴቶችን የበታችነት የማይቀበል ብሎም ጠለፋና አስገድዶ መድፈርን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡ መንግስት እና ባለድርሻ አካላት ብሎም እያናዳናዳችን ሰላም ለሴቶች እና ህጻናት ያለውን ዋጋ በመረዳት ለእናቶቻችን፤ ሴት ልጆቻችን እና እህቶቻችን ስንል ሁላችንም እንደዜጋ የበኩላችንን ለማበርከት ሀላፊነት አለብን፡፡ የዕለቱ መልእክት ነው፡፡