COVID-19 Response
 

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የፀረ-ሙስና ሥነ-ምግባር እና የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀንን በጥምረት አክብሮ ዋለ፤

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሰራተኞች 33ተኛውን ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ ኤድስ ቀን እና ለ 16ኛ ጊዜ የተከበረውን የፀረ-ሙስና እና ሥነ-ምግባር ቀን በእንስቲትዩቱ ዋናው መስሪያ ቤት ሂሩይ አዳራሽ አክብረው ውለዋል፡

 ኤች አይ ቪ ኤድስ በሀገራችን ላለፉት ሶስት አስርት አመታት አያሌ ህዝቦችን ለህልፈት በመዳረግ ሁለንተናዊ ቀውስን ስያደርስ መቆየቱ እና እስካሁንም መድሀኒት አልባ በመሆን የአለም አቀፍ  ስጋት ሆኖ እነደቀጠለ ነው፡፡ በመሆኑም አለም የዚህን በሽታ አለማቀፋዊ  ስጋትነትን በማሰብ “ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመግታት አለማቀፋዊ ትብብር የጋራ ሀላፊነት” በሚል መርህ መሪ ቃል ቀርጾለት አከብሮ ውሏል፡፡

 የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬከረተር ዶ/ር ዲሪባ ገለቲ በበአሉ ላይ በመገኘት ፕሮግራሙን የከፈቱ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸውም  የዘንድሮውን የኤች አይቪ ኤድስ እና ሥነ-ምግባር ቀን ከሌላውየሚለየውኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት ተጨማሪ ትጋትና ጉልበት በተጠየቅንበት ወቅት ላይ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡ዳይሬክተሩ አያይዘውም የምርምሩን እና የግብርናውንአምራችዜጋ እነዚህ ተደራራቢ ተግዳሮቶች ወደኋላ እንዳያስቀሩት ከፍተኛ ስራ እናጥንቃቄያስፈልገናል በማለት ጨምረው  ገልጸዋል፡፡

 በፕሮግራሙ ላይ ከበአሉ ታዳሚዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የኤችአይቪ ኤድስ አለም አቀፋዊና አገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ለተሰብሳቢውቀርቧል፡፡በዚህም በአለምደረጃ እስካሁን ቫይረሱ መኖሩ ከታወቀ እ.ኤ.አ 1981.ም ጀምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸ ሲሆን በየዓመቱ 1.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚያዙ ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡ እንደ ሀገር ደግሞ በአሁኑ ሰዓት 600  ሺህ በላይ ዜጎቻችን ኤች አይቪ ኤድስ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም  የእንስቲትዩቱ ሰራተኞች  እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በመጠበቅ የዚህን አስከፊ በሽታ ስርጭት እንዲከላከሉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራም ተሰርቷል፡፡

የፀረ-ሙስና እና ሥነ-ምግባር ቀን ምክንያት በማድረግም ብልሹ አሰራር እና ሙስና በሀገር ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ በሰፊው ተብራርቶ የቀረበ ሲሆን መሪ ቃሉም  ‹‹ የትውልድ የሥነ-ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፕሊን በመምራት፤ሌብነትንና ብልሹአሰራርን በመታገል የብልፅግና ጉዟችንን እናፋጥናለን! ››  የሚል ነው፡፡

ወ/ሮ ተናኘ ኪዳኔ የፀረ-ሙስና እና ሥነ-ምግባር ዳይሬክተር በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያለ አድሎ ሐቅን፣ እውነትን መሰረት በማድረግ የመንግስት ስራን ሥነ-ምግባራዊና ህጋዊ መሰረት ባለው መንገድ ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የግንዛቤ ማስበጫ መድረኩም  ዋና ዋና የሙስና መገለጫዎች፣ ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት እና ተፈፅሞ ሲገኝ የሚያስከትለው ተጠያቂነት ላይ ያተኮረ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ የእንስቲቲዩቱ ሰራተኞችም እራሳቸውን ከሙስና በማራቅ ለሌሎች  አርዕያ እንዲሆኑም ጨምረው አሳስበዋል፡፡   

በመጨረሻም በአሉን  በዓመት አንድ ጊዜ ቀኑን በማሰብ ማክበር ብቻ ሳይሆን ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ለአንድም ቀን እረፍት የማይሰጠን ብርቱ ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ አለብን፡፡ ለማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁልጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ድህነት፤ በሽታን እና ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር  ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ፡፡ብሎም ብልሹ አሰራሮችን ለመግታት ‹‹እኔ ምን ጠጠር አስቀምጬአለሁ?›› ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፤ የተግባር ሰው በመሆን ለህሊናችን እረፍት የሚሰጠንን መልስ ለመስጠት የተዘጋጀን እንሁን፡፡ የዕለቱ መልእክት ነው፡፡